1.
ስላንድ አገር ሰማሁ
ከሩቅ ጠረፍ ያለ
መልካም የተዋበ ግሩም ቤት
የሠ ራው የሱስ ነው
ከዚያ አንሞትም ከዚያ
ፈጽሞ አናረጅም
ከዚያ መድከም ማርጀት የለም
ከዚያ አገር ከቶ አንደክምም
ከዚያ መድከም ማርጀት የለም
ከዚያ አገር ከቶ አንደክምም
2.
ከዚያ ውብ ቤታችን
አንንከራተትም ሁላችን እንደሰታለን
ለንጉሡ ክብር እንዘምራለን
ሞት የሌለበት ውብ አገር ነው
3.
ሥራችን ሲፈጸም አክሊልን ስናገኝ
ችግራችንንም ሁሉ ሲያልቅ
ሐዘናችን ያልፋል ድምፃችን ይሰምራል
ሁላችን ባንድ እንሆናለን
4.
ቶሎ ገለል እንበል ከአድካሚው ሥራ ወደ ወርቃማዋ ከተማ
ደስታን እንካፈል ሁላችን ባንድ ላይ
ድካም ከሌለበት መኖሪያ