1.
በዮርኖስ ወንዝ ዳር ቆሜ
አሻግሬ ስመኝ
የምታምረውን ከንዓንን
ለኔ እመኛታለሁ
ባመረችው ሥፍራ ዕረፍት ስናገኝ
ወደ ለምለሟ ልንሻገር
የበጉንም መዝሙር እንዘምራለን
ከየሱስ ጋር እንኖራለን
2.
በተዘረጋው ሜዳ ላይ
ታላቅ ቀን ያወጣል
የሱስ ጌታችን ይነግሣል
ጨለማን ያጠፋል
3.
3. ከዚያ ከሚያስደስት ሥፍራ
መቼ እደርሳለሁ
አብን መቼ አየዋለሁ
በክንዱስ አርፋለሁ
4.
ልቤም በደስታ ተሞልቷል
ከዚህ ብዙ አልቆይም
ዮርዳኖስም ቢሞላብኝ
በድፍረት ልሔድ ነኝ