ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #221h / Song #221h

ቅርብ ነው ጊዜው

There's a Land that is Fairer than Day

ምድብ / Category: የሰማይ ቤት / Heavenly Home
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የምታምረው ሀገር ያች ናት
በእምነት በሩቅ የምናያት
አባታችን በዚያ ይሆናል
መኖርያም ያዘጋጅልናል
ቅርብ ነው ጊዜውም
ልንገናኝ በሰማይ አገር
ቅርብ ነው ጊዜውም
ልንገናኝ በሰማይ አገር
2.
በዚያ ድንቅ አገር ልንዘምር
የቅዱሣንን ግሩም መዝሙር
መንፈሳችን ከቶ አያዝንም
ለዘላለምም አንደክምም
3.
ለባለ ፀጋው አምላካችን
ምስጋናችን እናቀርባለን
ስለ ታላቅ የፍቅር ስጦታው ስለማይለየንም ፀጋው
100%
100%