ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #291h / Song #291h

በዚያ ሌሊት ተዘምሯል

It Came Upon the Midnight Clear

ምድብ / Category: ልደት / Christmas
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
በዚያ ሌሊት ተዘምሯል
ሰማያዊ መዝሙር
በመላእክት ወርቅ በገና
ላለንባት ምድር
ሲሉ ሰላም ለሁላችሁ
መልካም ፈቃድ ከላይ
ዓለምም በሰላም አርፎ
ይሰማቸው ነበር
2.
በጸጥታ ከላይ መጥተው
በክንፋቸው በርረው
የዘመሩት ታላቅ መዝሙር
ዓለምን አነቃው
ላዘነችው ለዚች ዓለም
ከሰማይ ላይ ወርደው
ያፈሰሱት የደስታ ቃል
ሰላምዋን መለሰው
3.
እናንት ችግር የያዛችሁ
ኃጢአት ያጠቃችሁ
ለምን ባሳዛኙ መንገድ
ላይ ትጓዛላችሁ
ተመልከቱ ወርቁን ጊዜ
ቸኩሉ በደስታ
የመላእክትንም መዝሙር
ኑ ስሙ በርጋታ
4.
ጊዜው አሁን ተፈጽሟል
የነቢያት ትንቢት
ዘመን መጥቶ ዘመንም ሲያልፍ
ደረሰ ወርቁ ዓመት
ሰላም ሲጐርፍ በምድር ላይ
ክብሩን ሲዘረጋ
ዓለምም ሁሉ ይዘምር
ተሰጥቶታል ጸጋ
100%
100%