ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #44h / Song #44h

ካለህ የበለጠውን ስጥ

Give of Your Best to the Master

ምድብ / Category: ንሥሐ / Repentance
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ካለህ የበለጠውን ስጥ
ወጣትነትህንም
ሁለመናህን አስረክብ
ለእውነት ወታደር ሁን
የሱስም ምሳሌህ ሆኖ
ራሱን ላምላክ አስገዛ
አንተም ለጌታ ታማኝ ሁን
የበለጠውን ስጠው
ካለህ የበለጠውን ስጥ
ወጣትነትህንም
ያምላክን ጦር ዕቃ ልበስ
እውነትን ይዘህ ገስግስ
2.
ካለህ የበለጠውን ስጥ
ልብህ ለጌታ ይሁን
በአገልግሎትህ ሁሉ
ጌታህን አስቀድመው
አምላክ ወዶህ ልጁን ሰጠህ
ጽድቁንም አበራልህ
የአምላክን ፍቅር አስብ
የበለጠውን ስጠው
3.
ካለህ የበለጠውን ስጥ
ወዶናል ይገባዋል
ላንተ ሲል ሕይወቱን ሰዋ
የሰማይ ክብሩን ተወ
ሐፍረትህንም ወሰደ
ጽድቁንም ላንተ ሰጠ
ውለታውን ሁሉ አስብ
የበለጠውን ስጠው
100%
100%