ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #48h / Song #48h

የየሱስ ድምጽ ሲለኝ ሰማሁ

I Heard the Voice of Jesus Say

ምድብ / Category: ንሥሐ / Repentance
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የየሱስ ድምጽ ሲለኝ ሰማሁ ና ወደ ዕረፍቴ
አንተ የደከመህ ሰው ሆይ ዕረፍ በብብቴ
ወደርሱ መጣሁ በድካም በኃዘንም ሳለሁ
እርሱ ደስታን ስለ ሰጠኝ ዕረፍትን አገኘሁ
2.
የየሱስ ድምጽ ሲለኝ ሰማሁ
እነሆ ሰጠሁህ
የሕይወትን ውኃ ጠጣ
አንተ የተጸማህ
ወደርሱ መጣሁ
ሕይወትን ከሚሰጠው ጠጣሁ ነፍሴ ከሕይወት ምንጭ ረካች በርሱም እኖራለሁ
3.
የየሱስ ድምጽ ሲለኝ ሰማሁ የዓለም ብርሃን ነኝ
ብርሃንህ ይወጣልሃል
እኔን ተመልከተኝ
ወደርሱም አየሁ
ፀሐዬን ኮከቤን አገኘሁ
ጉዞዬ እስከሚፈጸም
አብረን እንሔዳለን
100%
100%