ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #45h / Song #45h

ያለ ደስታ ስኖር

Just as I Am

ምድብ / Category: ንሥሐ / Repentance
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ያለ ደስታ ስኖር ሳለሁ
ክቡር ደምህ ፈሰሰልኝ
ምሕረትህን ላገኝ መጣሁ
የአምላክ በግ መጣሁ እርዳኝ
2.
ከጨለማ ልዳን ብዬ
ሳልዘጋጅ ለጌታዬ
ጊዜያቱ አለፈብኝ
የአምላክ በግ ና ውሰደኝ
3.
በምድር ተንገላትቼ
በችግርና በጭንቀት
እንደዚህ ኖርሁ ተዋግቼ
ና ና አድነኝ ከጭንቀት
4.
መጣሁ ትቀበለኛለህ
ይቅርታን ትሰጠኛለህ
ያንተን ተስፋ አምነዋለሁ
የአምላክ በግ መጣሁ መጣሁ
5.
አሁን ያንተ ፍቅር አለኝ
ጠላቴን አሰወግድልኝ
የአንተ ነኝ ያንተ ብቻ
አሁን መጣሁ ተቀበለኝ
100%
100%