1.
ከአምላክ ርቄ ዙርያለሁ
አሁን ተመለስሁ
በኃጢዓት መንገድ ሄጃለሁ
ጌታ ሆይ መጣሁ
ወደ ቤት መጣሁኝ
አልዞርም በቃኝ
እጆችህን ዘርጋልኝ
ጌታ መጣሁኝ
2.
ክቡር ዘመናት አባከንሁ
አሁን ተመለስሁ
በመራር እንባ ተጸጸትሁ
ጌታ ሆይ መጣሁ
3.
በኃጢዓቴ ብዛት ደከምሁ
አሁን ተመለስሁ
ቃልህን ፍቅርህን አምናለሁ
ጌታ ሆይ መጣሁ
4.
የሚያነጻ ደምህን ስጠኝ
አሁን ተመለስሁ
ከበረድ አብልጠህ አንጻኝ
ጌታ ሆይ መጣሁ