ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #54h / Song #54h

እኔ የሱስን ለማየት

Brightly Beams Our Father's Mercy

ምድብ / Category: ንሥሐ / Repentance
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
እኔ የሱስን ለማየት
ከቶ አይሆንልኝም
የኔ ጠባይ ደካማ ነው
የሚመራኝ ለጥፋት
ብርሃንን ለሁሉ ፍጥረት
አብራልን ለሕይወት
በዚህ ብቻ እመራለሁ
በብፅናህ ለመግባት
2.
እንዴት ያለ ሕይወት ሆነ
ለተያዙ በመርገም
ከመከራ ቀንበር ሁሉ
በሞተበት ቀን ወጡ
ስለዚህ ይጠራል አሁን
በደሙ የተገዙን
እየው እየው ጊዜ ሳለ
ጨለማ ባይደርስብህ
3.
ማነው አሁን የሚጠራ
እየጮኸ በፍቅር
ወደኔ ኑ ኑ ሁላችሁ
ፀጋዬን ተቀበሉ
እርሱ ነው መድኃኒታችን
ስለ ዓለም የሞተ
ስለዚህ መጥራቱን አክብር
ለዘላለም ልትድን
100%
100%