ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #71h / Song #71h

ነፍሴን ተናገር

Speak to My Soul

ምድብ / Category: ጸሎት / Prayer
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
1.
ነፍሴን ተናገር የሱስ
ቀስ ብለህ ንገረኝ
በቸርነት አስታውቀኝ
አልተውህም በለኝ
እንዳዳምጥህ ልብ ስጠኝ
ቃልህን እንድሰማ
ነፍሴ ምስጋና ትምላ
ባንተም ደስ ይበለኝ
በለዘብታ ንገረኝ
በፍቅር ንገረኝ
ታሸንፋለህ በለኝ
ነጻም ትወጣለህ
በየቀኑ ንገረኝ
ሁልጊዜ አስታውሰኝ
አሁን ቃልህን ልስማ
አልተውህም ስትል
2.
ልጆችህን ተናገር
መንገድህን ምራቸው
በደስታም ምላቸው
ጸሎት አስተምራቸው
ሕይወታቸውን ቀድስ
ላንተ ሁሉን ይስጡህ
መንግሥትህን ያፋጥኑ
አንተን እስክናይህ
3.
እንደጥንቱ ተናገር
ምኞትህ ይገለጽ
ተግባሬን ሁሉ ልወቅ
ፈቃድህን ልፈጽም
ምራኝ አከብርህ ዘንድም
ክብርህን እንዳሳይ
በደስታ እንድታዘዝ
ሰርክም እንዳከብርህ
100%
100%