1.
አምላኬ ወዳንተ እቀርባለሁ
ሸክሜ እንኳ ቢከብድ ከነሸክሜ
አሁንም መዝሙሬ
ወዳንተ መቅረብ ነው
ወዳንተ መቅረብ ነው
አምላኬ ሆይ
2.
ሣላስበው ቀኑ ከንቱ ሔደ
ጨለማ ከበበኝ በበረሃ
በሕልም እንኳ ሆኜ
አምላኬ ወዳንተ
አምላኬ ወዳንተ
እቀርባለሁ
3.
የሰማይን መንገድ ግለጥልኝ
በምህረትህ ሁሉን ስደድልኝ
መላክትህ ያድሙኝ
አምላኬ ወዳንተ
አምላኬ ወዳንተ
እቀርባለሁ
4.
በነቃ ኃሣቤ ሣመሰግን
ከኃዘኔ ሥፍራ ቤቴን ልሥራ
ጩኸቴን ለማቅረብ
አምላኬ ወዳንተ
አምላኬ ወዳንተ
እቀርባለሁ
5.
ከዚህ በደስታ ወደ ሰማይ
ለመሔድ በእልልታ እበራለሁ
መዝሙሬን ስዘምር
አምላኬ ወዳንተ
አምላኬ ወዳንተ
እቀርባለሁ