ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #70h / Song #70h

በመከራ ጊዜ

In the Hour of Trial

ምድብ / Category: ጸሎት / Prayer
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
በመከራ ጊዜ የሱስ አስበኝ
በክህደቴም ምክንያት እንዳትለየኝ
እምነቴ መድከሙ በመልኬ ሲታይ
አትተወኝ ጌታ ካንት እንዳልለይ
2.
በማይጠቅም ደስታ ዓለም ያታልላል በተንኮልም ወጥመድ ሰውን ያጠምዳል አስታውሰኝ ያን ጊዜ ጌተሰማኔን ደግሞም ቀራንዮን የሾህ አክሊልህን
3.
ሐዘንን ችግርን በምህረት ብትሰድ
ሕመም ቢደርስብኝ ወዳንተ ስሄድ
አደራ ጌታ ሆይ እጅህ ይታየኝ
ችግሬን ስነግርህ አምላክ ደግፈኝ
100%
100%