1.
ያምላክ ወዳጆች ኑ
ደስታችሁ ትታወቅ
ኑ ባንድነት እንዘምር
ላምላካችን ቅዱስ መዝሙር
የርሱን ዙፋን ከበን
እናንግሠው በክብር
ወደ ጽዮን እንጓዝ
ወደዘያች ኢየሩሳሌም
እንገስግስ ወደ ጽዮን
ወዳምላካችን ከተማ
2.
እናንተ እምቢተኞች
ተነሡ ዘምሩ
የኛን አምላክ የማታውቁ
ኑ ከርሱ ጋራ ታረቁ
የጌታ ልጆች ግን
ደስታችሁ ትታወቅ
3.
እንግዲህ እንዘምር
እንባችንም ይድረቅ
ባማኑኤል መንገድ ላይ ነን
ድንገት ፈርተን እንዳንወድቅ
ስንጓዝ ወደርሱ
ወዳማረው አገር