1.
ከየሱስ ጋር በደኅና እሔዳለሁ
በዚህ ዓለም ላይ በርሱ ከተመራሁ
ያለርሱ ደስታዬ ከንቱ ይሆናል
እርሱ ግን ፍርሃትን ሁሉ ያጠፋል
ምንጊዜም ምንጊዜም
ከቶ አልፈራም
ከየሱስ ጋር በደኅና
እሔዳለሁ
2.
የሱስ ክርስቶስ ከኔ ከቶ አይርቅም
ሌላ ወዳጅ ሲረሣ አይረሣኝም
እጆቹ በጭንቁ መንገድ ቢመሩኝ
ከርሱ ዘንድ የምስጋና ቤት አለልኝ
3.
ከየሱሴ ጋር በሰላም አርፋለሁ
በሌሊት ጨለማ ስከበብ ሣለሁ
በደስታ እንደምነቃም አውቃለሁ
በሚያምረውም ቤት አብሬ እኖራለሁ