1.
ወደ ጸሎት ስፍራ መጣሁ
መልድ ብዬ ጤዛው ሣይረግፍ
ከዚያ ስገባ ድምፅህን ሰማሁ
ያምላክ ልጅ ሲመጣ አየሁ
ከኔ ጋር ሲጓዝ ሲያነጋግረኝ
የራሱ እንደሆንሁ ሲነግረኝ
አብረንም ሣለን ደስታ አገኘን
ማንም ያላገኘውን
2.
ሲናገር የድምፁ ማማር
አቆመው የዖፎችን መዝሙር በዚሁም ጊዜ ዜማን አሰማኝ
ሁልጊዜ የማይረሳኝ
3.
አብሬው እቀመጣለሁ
ቀን አልፎ ጨለማ ቢሆንም
ፈተናን እንዳልፍ ይፈልገኛል
በየዋህ ድምፅ ይጠራኛል