ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #80h / Song #80h

የሱስ የምር ወዳጄ ነው

Jesus is all the World to Me

ምድብ / Category: የክርስቲያን ኑሮ / Christian Life
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የሱስ የምር ወዳጄ ነው
ተስፋዬ ሕይወቴም
ብርታቴ ነው በየቀኑ
ያለ እርሱ እወድቃለሁ
ባዘንሁ ጊዜ ይቀርበኛል
መጽናናትም ይሰጠኛል
ባዘንሁ ጊዜ ደስታዬ ነው
ወዳጄ
2.
የሱስ የምር ወዳጄ ነው
በችግር ረዳቴ
በረከትን ከርሱ እሻለሁ
እርሱም ይሰጠኛል
ዝናም ፀሐይን ይልካል
ደግሞም ወርቃዊ አዝመራ
በረከቱን ይሰጠኛል
ወዳጄ
3.
የሱስ የምር ወዳጄ ነው
ታማኙ እሆናለሁ
እርሱም ለኔ ታማኜ ነው
እንዴት እክደዋለሁ
እከተል ዘንድ ይገባኛል
በሌት በቀን ይመራኛል
መከተል ነው ቀንና ሌት
ወዳጄን
4.
የሱስ የምር ወዳጄ ነው
ሌላም አያሻኝም
አምነዋለሁ ዓለም እስኪያልፍ
አሁንም አምነዋለሁ
ከርሱ ጋራ መኖር ውብ ነው ደግሞም ፍጻሜ የለውም
የዘላለም ደስታ ህይወት
ወዳጄ
100%
100%