1.
የሱስ ክርስቶስ የኔ ወዳጅ
እንደ እርሱ የለኝም
ሌሎችም እንኳ ቢተውኝ
እርሱስ አያደርገውም
ማን ነው አሁን የሚለየኝ
ጌታዬ ከወደደኝ
አንድነት ከእርሱ አለኝ
ማንም የማይወስድብኝ
2.
እርሱ ሞተ ስለ እኔ ማን ነው የሚፈርድብኝ
ከአባቱ ለመነልኝ
ለዘላለም ጠቀመኝ
ማን ነው አሁን የሚከሰኝ
እርሱ ራሱ መረጠኝ
ማን ነው ከርሱ የሚነጥቀኝ
ጌታዬ ሲጠብቀኝ
3.
ፍጹም ተስፋ አሁን አለኝ
ሞትም ሆነ ሕይወትም
ከጌታዬ አይለየኝም
ራብም ሆነ ጭንቀትም
ዝቅታም ከፍታም ኃዘን ችግር
አላፊ መጭም ቢሆን
ከዚህ ፍቅር አይለየኝም
በየሱስ ያገኘሁት