ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #85h / Song #85h

ልረፍ በየሱስ ክንዶች

Safe in the Arms of Jesus

ምድብ / Category: የክርስቲያን ኑሮ / Christian Life
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ልረፍ በየሱስ ክንዶች
ልረፍ በደረቱ
በፍቅሩ ከከለለኝ
ነፍሴ አትፈራም ከቶ
ስማ ከሰማይ መዝሙር
በመላእክት ሲዘመር
በክብር የሚዘመር
በብርጭቆ ባሕር
ልረፍ በየሱስ ክንዶች
ልረፍ በብብቱ
በፍቅሩ ከከለለኝ
ነፍሴ አትፈራም ከቶ
2.
ልረፍ በየሱስ ክንዶች
ልረፍ ከሰቀቀን
ልረፍ ካለም ፈተና
ከኃጢዓትም ጭምር
ከኃዘን ነፃ ልንሆን
ደግሞም ከጥርጣሬ
ለጥቂት ጊዜ ብቻ
እንሰቃያለን
3.
የሱስ የነፍሴ አምባ
ስለኔ ሞተሃል
እምነቴ በዚህ አምባ
ለዘላለም ጸንቷል
ስለዚህም ልታገሥ
ጨለማ እስኪጨረስ
የምታምረውም ንጋት
እስክትመ ጣ ድረስ
100%
100%