ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #93h / Song #93h

ስትጨነቅ ሳለህ የሱስን ጥራ

Call to Jesus in Trouble

ምድብ / Category: የክርስቲያን ኑሮ / Christian Life
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ስትጨነቅ ሳለህ ጥራ የሱስን
ከጥፋት ሁሉ ለመዳን
ያለህን ድካም ግለጽለት አሁን
ችግርህን ሁሉ ንገረው
በአዳኝ ፀጋው ያጠነክርሃል
ግን ባንተ ሥራ ፈጽመህ ሙተሃል ስለዚህ ቶሎ ወደ የሱስ ቸኩል
የፀጋ ኃይሉን ተቀበል
2.
አምላካችን ኃዘንን ሁሉ ያያል የልብን ጩኸት ይሰማል
የሚያድስ ኃይልም ይሰድልሃል በእምነት ብቻ ተቀበል
3.
ባጭሩ ዘመን በእንግድነት ኑሮህ ጨለማ ብቻ የሞላ
ወደ ላይ አሻቅበህ የሱስን እይ ጨለማውንም ያጠፋል
100%
100%