1.
የሱስን ትቼ ዓለምን ባተርፍ
የእለት ሕይወቴ ጥቅመ ቢስ ነው
በሃብቴ ብዛት እረፍት የለኝም
ልቤም ሰላምን አያገኝም
የሱሴን ትቼ ዓለምን ባተርፍ
ጥረቴ ሁሉ አይረባኝም
ይልቅ የሱስን የኔ ባደርገው
ለልቤ ሰላም አገኛለሁ
2.
ሰዎች ቢያፈቅሩኝ ሐብቴም ቢበዛ ስሜንም ደግሞ ቢያከብሩልኝ
ተስፋም ባይኖረኝ ልሠራ ወደብ
ተጉዤ ሄጄ የት ላርፍ ነኝ
የሱሴን ብክድ የሞተልኝን
መስቀሉን ብጥል ያዝ ያለኝን
ጌታ ሲገለጽ ባሰቃቂው ቀን
ማንም አይችልም እኔን ሊያድን
3.
አልችልም እኔ ልኖር ብቻዬን
ያለ የሱሴ በዚች ዓለም
መንገዴ ያለ እርሱ ይጨልማል
ልቤም በሐዘን ይጨነቃል
ብኖርስ እንኳ ያለ መድህኔ
በጠራኝ ጊዜ ምን ይዋጠኝ
በሌላ መንገድ ልሄድ ብሞክር
ሕይወት የለኝም ለዘላለም
4.
የየሱስ መሆን ታላቅ ደስታ ነው
ልብ የሚፈውስ ቸር አዳኝ ነው
ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ይለኛል
ልቤን በደሙ ያጥብልኛል
የሱስን ብይዝ የሱሴን ብቻ
ምንም ባልፈልግ ከርሱ ሌላ
የሚያሰፈልገኝን ይሰጠኛል
ለዘላለም ይጠብቀኛል