ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #107h / Song #107h

በክንፉ ሥር

Under His Wings

ምድብ / Category: መታመን / Trust
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
በክንፉ ሥር በደህንነት አርፋለሁ
ጨለማና ሞገድ ቢከፋብኝ
እንደሚያድነኝ አሁንም አውቃለሁ
ዋጅቶኛልና እኔም ልጁ ነኝ
በክንፉ ሥር በክንፉ ሥር
የተጠጋ አይጐዳም
በክንፉ ሥር
ነፍሴ ታርፋለች ዘላለም
ትጸናለች
2.
በክንፉ ሥር ላዘኑ ዕረፍት አለ
እኔም ከዚያ ዕረፍት አገኛለሁ
ዓለም ድካሜን ልትፈውስ ሳትችል
ደስታ አለኝ በርሱም እጽናናለሁ
3.
በክንፉ ሥር እንዴት ያለ ደስታ ነው
እጠጋለሁ እዚያ ለዘላለም
በክንፉ ልጠበቅ እንዳልጐዳ
በየሱስ አርፋለሁ ለዘላለም
100%
100%