ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #119h / Song #119h

የሱስ እየመራኝ ሳለ

All the Way My Saviour Leads Me

ምድብ / Category: መታመን / Trust
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የሱስ እየመራኝ ሳለ
ምን መጠየቅ ያሻኛል
ምሕረቱን እንዴት ልካደው
እስካሁን የመራኝን
ሰማያዊ ሰላም ምቾት
ከርሱ ጋር ስኖር ሳለሁ
ከሚመጣብኝም ሁሉ
የሱስ ይጠብቀኛል (2 ጊዜ)
2.
የሱስ የሚመራኝ መንገድ
እጅጉን ደስ ያሰኛል
ፀጋውንም ይሰጠኛል
ሕያው ምግብ ይሰጣል
ከድካሜ ሊያበረታኝ
ነፍሴም እንዳትፀማ
መንፈሱን ያፈልቅልኛል
በደስታም ያጠጣኛል (2 ጊዜ)
3.
የሱስ የሚመራኝ መንገድ
ፍቅር የተሞላ ነው
ተስፋዬም ፍጹም ዕረፍት ነው
በሰማይ ቤቴ ያ ለው
ወደ ሰማይ እበራለሁ
ከእንቅልፌ ስነቃ
ምራኝ በዕድሜዬ ሁሉ
ይህን ነው የምዘምር (2 ጊዜ)
100%
100%