ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #121h / Song #121h

ስለ ነገው ምንም አላውቅ

I Don't Know About Tomorrow

ምድብ / Category: መታመን / Trust
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ስለ ነገው ምንም አላውቅ
በየቀኑ እኖራለሁ ብርሃኑንም
አልዋስም ሰማዩ እንዳይጨልም
ስለ መጪው አላስብም
የጌታን ቃል አውቃለሁ
ከርሱ ጋራ እሄዳለሁ
የወደፊቱን ያውቃል
ያን ሁሉ የነገ ጣጣ
የማውቀው አይመስለኝም
ግን ባለቤቱን አውቃለሁ
ዛሬንም ያቆመውን
2.
ጎዳናውም ሁሉ በርቷል
ደረጃውን ስወጣ
ችግሩ ሁሉ ተቃሏል
ደመናውም ተገልጧል
ከዚያ ችግር አይገኝም
ከዚያም ባይን እንባ የለም
በተቀደሰችው አገር
ሁል ጊዜ እንኖራለን
3.
የነገውን ምንም አላውቅ
ያደኸየኝ ይሆናል
ግን ወፏን የሚመግባት
ባጠገቤ ይቆማል
የኔም ፈንታ ጎዳናዬም
ነበልባል ወይም ጎርፍ ነው
ሆኖም እርሱ ከኔ ጋር ነው
በደሙም ተሸፈንሁ
100%
100%