1.
ጌታን ማመን ደስ ያሰኛል
ቃሎቹንም መቀበል
ወደ ተስፋው ይጠራናል
እርሱም ብሎዋል እወቅ
የሱስ የሱስ አምንሃለሁ
ስለ መልካሙ ሥራህ
የሱስ የሱስ ክቡር የሱስ
ባንተ አምንብህ አለሁ
2.
ጌታን ማመን ደስ ያሰኛል
በተቀደሰው ደሙ
በእምነት ብቻ መታጠብ
ከርሱ በፈሰሰው ደም
3.
ጌታን ማመን ያስደስታል
ከኃጢዓት ነፃ መሆን
ሕይወት እረፍት ደስታ ሰላም
ከየሱስ በመቀበል
4.
ስላመንሁህ ደስ ይለኛል
አዳኜ ክቡር የሱስ
ከኔ ጋር ነህ ይሰማኛል
እስከ ፍፃሜ ድረስ