1.
ያምላክን ጸጋ አላውቅም
የገለጠልኝን
የክርስቶስን ፍቅርም
ለርሱ የዋጀኝን
ግን አውቃለሁ የአመንሁትን
አውቃለሁ ችሎት እንደተሰጠው
ከኃጢአት እንዲጠብቀኝ
እስከ መገለጡ ቀን
2.
አላውቅም እንደ ምን ሰጠኝ
አዳኙን ሃይማኖት
እንዴትም እንዳሳመነኝ
ትርፍ ያለውን እምነት
3.
አላውቅም መንፈሱ እንዴት
በሰው እንዲሠራ
እየገለጠ የሱስን
እየሰጠ እምነትን
4.
የጌታን መምጫ አላውቅም
ቀትር ቢሆን ማታም
እንዴት እንድሄድ አላውቅም
በግር ይሁን ባየር