ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #118h / Song #118h

ከጌታ ጋር ስንሄድ

When We Walk with the Lord

ምድብ / Category: መታመን / Trust
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ከጌታ ጋር ስንሔድ
ቃሉ እያበራልን
እንዴት ያለ ክብር ይሰጣል
ፈቃዱን ስንፈጽም
አብሮነ ይኖራል
ከሚያምኑት ሁሉ ጋር ይሆናል
እንታመን እርሱን እንታዘዝ
ሌላ መንገድ የለንም
ሰላምን የሚሰጥ
2.
ጨለማ አይሆንም
ደመናም አይመጣም
ፈገግታ ጨለማን ያርቃል
ፍርሃት ጥርጥርም
ኃዘን እንባም የለም
ስንታዘዝ እና ስናምነው
3.
ሸክም የለብንም
ኃዘን አይነካንም
እንደ ሥራችን ይከፍለናል
ጥፋት ኃዘን የለም
ፊታችን አያዝንም
ስንታዘዝ እና ስናምነው
4.
የፍቅሩን ደስታ ግን
ልናውቀው አንችልም
ለርሱ ሳንሰጠው ልባችን
ምሕረትና ደስታ
ፀጋና ፍቅሩንም
ለሚታመኑት ነው የሚሰጥ
5.
በቅዱስ አንድነት
አብረን ስንቀመጥ
ከርሱ ጋራ አብረንም ስንሔድ
ሕጉን እየሠራን
ከርሱ ጋር ስንኖር
እርሱም ከሚያምኑት ጋር ይሆናል
100%
100%