ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #142h / Song #142h

የሚያስደንቅ መድህን

A Wonderful Saviour is Jesus My Lord

ምድብ / Category: ሰላም / Peace
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የሚያስደንቅ መድህን ነው የሱስ ጌታ
አስደናቂ አዳኜ ነው
ለነፍሴ ደግሞ መጠጊያዋ ነው
የደስታን ወንዝ ባየሁ ጊዜ
ለነፍሴ መጠጊያ ይሆንላታል
ከጥማቷም ያረካታል
ነፍሴን በፍቅር ጥላ ያስጠጋታል
በጆቹም ይጋርዳታል
በጆቹም ይጋርዳታል
2.
የሚያስደንቅ መድህን ነው የሱስ ጌታ ሸክሜንም ያቀልልኛል እንዳልቸገር እርሱ ረዳቴ ነው የርሱን ብርታት ይሰጠኛል
3.
ቁጥር የሌለው በረከት ይሰጣል ባምላካዊ ኃይል ይሞላል ክብር ምስጋና ላምላካችን ይሁን
እንዲህ ያለ አዳኝ ለሰጠን
4.
ክብሩን ለብሼ በተነሣሁ ጊዜ ልገናኘው በደመና
አስደናቂ ፍቅሩን እዘምራለሁ ከብዙዎች ጋር በምስጋና
100%
100%