ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #145h / Song #145h

የሱስ ወደድሁህ

My Jesus I Love Thee

ምድብ / Category: ፍቅር / Love
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የሱስ ሆይ ወደድሁህ የኔ ነህና
ኃጢአቴንም ሁሉ እተወዋለሁ
ክቡር አዳኜና መድኃኒቴ ነህ
ከቀድሞውም ይልቅ አሁን ወደድሁህ
2.
ፊት ስለወደድኸኝ እኔም ወደድሁህ
ኃጢአቴን በቀራንዮ ተሸከምህ
ስለ መጨነቅህ እወድህአለሁ
ከቀድሞውም ይልቅ አሁን ወደድሁህ
3.
በሞትና ህይወት እወድህአለሁ
እያመሰገንሁህ ነፍሴ እስካለች
ሞትም ሲመጣብኝ እንዲህ እላለሁ
ከቀድሞውም ይልቅ አሁን ወደድሁህ
4.
በሰማይ ፍጻሜ በሌለው ደስታ
አንተን ከዚያ ሆኜ አወድሣለሁ
መዝሙሬን በደስታ እዘምር አለሁ
ከቀድሞውም ይልቅ አሁን ወደድሁህ
100%
100%