1.
ወደድሁህ ወደድሁህ ወደድሁህ ጌታ ወደድሁህ አዳኜ ወደድሁህ ጌታዬ
ወደድሁህ ወደድሁህ
ታላቅ አምላክ ነህ
ሕይወትህን ሰዋህ እኔን ለማዳን
2.
ደስ አለኝ ደስ አለኝ በመልካም ሥራህ
ደስታዬ አያልፍም እስከ ዘላለም
መዝገቤን ለማየት እናፍቃለሁ ከመላእክቱና ከርሱ ጋር ልኖር
3.
መድኃኒቴ የሱስ ባንተ ተባረክሁ
ተስፋና ህይወቴ ደስታና ዕረፍቴ
ፍቅርህ ደስታዬ ነው ስምህ መዝሙሬ
ልብና ምላሴን ፀጋህ ያስተምረው