አስከ ዛሬ ድረስ አብረን ተጉዘናል ከጌታየ ጋራ ክፉ ደግ አልፈናል
ፍቅሩ ያው ያው ያው ነው ከቶ አልተለወጠም
ቁጥር 2 / Verse 2
ያደግሁባቸውን ቀየወች ሳያቸው
ያ የቀድሞ ውበት የታለ ለዛቸው
አንድ ነገር ብቻ አለ እንደ ትናንቱ
የእግዚአብሔር ፍቅር የሱስ የናዝሬቱ
ቁጥር 3 / Verse 3
ስፍገመገም ሲያየኝ ኃይሌ ሲከዳኝ
በዘመኔ ሁሉ እየዳሰሰኝ
አንድ ነገር ብቻ አለ እንደ ትናንቱ
የእግዚአብሔር ፍቅር የሱስ የናዝሬቱ
ቁጥር 4 / Verse 4
ያን ሁሉ በረሃ አብረን ስናቋርጥ
መልክና ውበቱ ቃናው ሳይለወጥ
አንድ ነገር ብቻ አለ እንደ ትናንቱ
የእግዚአብሔር ፍቅር የሱስ የናዝሬቱ