1.
ተቀምጦ በመንገድ ዳር ሲለምን
ዓይኑ ጠፍቶ አላየም ብርሃንን
ተራቁቶ በብርድም ሲንቀጠቀጥ
የሱስ መጣ ጨለማን ሊያስወግድ
የሱስ መጥቶ የሰይጣንን ኃይል ሊያፈርስ የሱስ መጥቶ እንባችንን ሊያብስ
ጨለማ አልፎ ህይወት በክብር ይሞላል
ሲመጣ ሳል ሁሉም ይለወጣል
2.
በቤት ባገር በርኩስ መንፈስ ተነድቶ
በቀብር ቦታ ኖረ ተሰቃይቶ
ጎዳ ራሱን በርኩስ መንፈስ ተይዞ
ጌታ ፈታው ሲኖር ሣል ተግዞ
3.
እርኩስ እርኩስ ነኝ
ሲል ጮኸ ልምጻሙ
ድዳ ደንቆሮም በስቃይ ቆሙ
ተቃጠሉ በበሽታ ተይዘው
የሱስ መጣ
ጠፋ ፍርሃታቸው
4.
ሰዎች ዛሬ አውቀው
የአምላክን ኃይል
ስላልቻሉ ኃጢአትን ለመግደል
አዝነው ሣለ ልባቸውም ተሰብሮ
የሱስ መጣ
ለመቀመጥ አብሮ