ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #158h / Song #158h

ያባትህ እጅ ተዘርግቷል

Jesus Bids us Come

ምድብ / Category: መድህን / Salvation
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ያባትህ እጅ ተዘርግቷል
ልጁን ሊቀበልህ
ገና በስምህ ይጠራል
ወደርሱም ይስብሃል
ገና ከፍ ያለ የምክር
ድምፁ ይነግርሃል
እያለ ልጄ ሆይ ስማ
በሰርጌ ቤት ግባ
2.
ያለ ሰላም የምትኖር በዓለም በረሃ
ያ ደረቅ ምንጭ የለበትም
ለማርካት የሚችል
ከርሱ የጠበቅህ እንደሆን
ጥማትህ ይረካል
ግን ሕይወት ያለበት የሱስ መድኃኒታችን ነው
3.
ያ ርስት በፊት ያገኘኸው
በአንተ ኃጢዓት
ሰይጣንን በማገልገልህ
ቀርቶብህ እንደሆን
አሁን ቢሆንም ይጠራል
ሊሰጥህ ርስትህን
ያጠፋኸው በኃጢዓትህ
ይመለስልሃል
4.
የጠፋ ልጅ ወዳባቱ
የመጣ እንደሆን
በዚያ ቤት ሙሉ ደስታ
ለሁሉ ይሆናል
ስማ እልልታ በሰማይ
ጠፍቶ የነበረ
ካባቱ ቤት የራቀ ልጅ
አሁን ተመልሷል
100%
100%