1.
የዘለዓለም ምርጫዬ ነህ
ወዳጄና ሕይወቴ
በጉዞዬ ካንተ ጋራ
ልራመድ መድኃኒቴ
ካንተ ጋር (4 ጊዜ)
በጉዞዬ ካንተ ጋራ
ልራመድ መድኃኒቴ
2.
ለዓለም ምቾትና ደስታ
ለዝናም ጸሎቴ አይሁን
በደስታ ልሰቃይ
ልሥራ ብቻ ካንተ ጋር ልሁን
ካንተ ጋር (4 ጊዜ)
በደስታ ልሰቃይ ልሥራ
ብቻ ካንተ ጋር ልሁን
3.
በሞት ጥላ ውስጥ ና ምራኝ
ባሕህሩንም አሻግረኝ
ወደ ዘለዓለም ሕይወት ደጅ
ጌታ ካንተ ጋር አግባኝ
ካንተ ጋር (4 ጊዜ)
ወደ ዘለዓለም ሕይወት ደጅ
ጌታ ካንተ ጋር አግባኝ