1.
የተከፈተ በር አለ
በርሱም ብርሃን ይወጣል
የመድኃኒታችን ፍቅር
በመስቀል ላይ ያሣያል
ጥልቅ ሆይ ከፀጋህ አምላኬ
ያ በር ተከፈተ ለኔ
ለኔ ለኔ
ተከፍቶልኛል
2.
ተከፈተ ለሁሉ ሰው
መድኃኒትን ለሚሹ
ለንጉሥም ለባርያም
ለምድር ወገን ሁሉ
3.
ስለዚህ ሒድ ወደዚያ ደጅ
በዚያ ግባ ሳይዘጋ
ዘውድ ለመቀበል አትዘግይ
የአምላካችን ፀጋ
4.
በሰማያዊ ደጅ አንድ ቀን
መስቀላችን ልንጥል
የሕይወት አክሊል ልንጭን
የሱስን ልናከብር