1.
ሁሉን ወስደህ ጌታን ስጠኝ
ያለም ደስታ ከንቱ ነው
ፍቅሩ ግን እስከ ዘላለም
ሳይለወጥ ይኖራል
የጸጋው ከፍታ ጥልቀት
የፍቅሩን ቁመት ስፋት
የማዳኑንም ሙሉነት ሰው አይችልም ሊገምት
2.
ሁሉን ወስደህ ጌታን ስጠኝ
የነፍሴን መልካም አጽናኝ
ባዝን እንኳን እዘምራለሁ
አዳኜ ከጠበቀኝ
3.
ሁሉን ወስደህ ጌታን ስጠኝ
የፊቱን ፈገግታ ልይ
በዚች ዓለም ስጓዝ ሳለሁ
ብርሃኑ ያጽናናኛል
4.
ሁሉን ወስደህ ጌታን ስጠኝ
እምነቴ መስቀሉ ነው
በሚያንጸባርቀው ብርሃን
የጌታን ፊት እስከማይ