1.
ነፍሶች ሁሉ በኃጢዓት
የተጨቆናችሁ
በውነት ጌታችን ፈዋሽ ነው
በቃሉ ብታምኑ
በርሱ ጽኑ በርሱ ጽኑ
በጌታ ጽኑ
ይቅር ባይ ነው
ይቅር ባይ ነው
መድኃኒታችን
2.
የሱስ ለኛ ሲል በመስቀል
ደሙን አፈሰሰ
ጥልቅ ከሆነውም ኃጢዓት
እርሱ ያነጻናል
3.
አዎን የሱስ መሪያችን ነው
ለረፍት የሚጠራን
በርሱ ብናምን ሳንዘገይ
ደስታ ይሰጠናል
4.
ወደርሱ እንሂድ በአንድነት
ወደ ክቡር ጌታ
በዚያችም ሀገር በደስታ
ከርሱ ጋር እንድኖር