1.
ታላቅ የመለኮት ፍቅር
ጥልቅና ሃያል ቅዱስ
ከየሱስ ልብ ይመነጫል
የማያልቅ ግሩም ፍቅር
ድንቅ የጸጋ በር ከፈተ
እኔ እንድገባበት
ዕዳዬን እርሱ ከፈለ
ኃጢአቴን ይቅር አለ
2.
ፍርሐት ውጦኝ ስጨቅ ሳል
ልቤም በጣም አዝኖብኝ
የሱሴ ግን አዘነልኝ
ልቅሶዬን ሁሉ ሰማኝ
3.
በዘላለም ፍቅሩ ወዶኝ
ሕይወቱንም ሰጥቶኛል
ኃጢያቴን ይቅር ብሎ
በደሙ አንፅቶኛል
4.
ግሩም ታላቅ አምላክ
አለኝ በጸጋው የቀረበኝ
የኔ አምባ መጠጊያ ነው
ለስሙ እዘምራለሁ