1.
ታላቁ ሐኪም መጥቷል
አዛኝ የሆነው የሱስ
ያዘነን ልብ ያስደስታል
እንስማ የጌታን ቃል
ስሙ ይላቅ ለቅዱሳን
ይወደስም በሰው ልሳን
ከመዝሙር ሁሉ ያምራል
የሱስ አዳኝ የሱስ
2.
ኃጢዓትህ ተሰረየልህ
የየሱስን ቃል ስማ
በሰላም ሂድ ወደ ሰማይ
አክሊል እንድትቀበል
3.
ክብር ይሁን ለሞተው በግ
አሁን አምንበታለሁ
መድኃኒቴን አከብራለሁ
የየሱስ ክርስቶስን ስም
4.
ስሙ ኃጢዓቴን ያጠፋል
ከየሱስ ሌላ የለም
ነፍሴ ለመስማት ደስ አላት
የየሱስ ክርስቶስን ስም
5.
ሲመለስ አክሊል ያመጣል
የሕይወትና ክብር
በመድህን ፊት ተቀምጠን
ይወራል ስለመዳን