1.
የሱስ መስቀልህን ልቅረብ
ያንን የክብር ምንጭ
ከዚያ ነፃ ምንጭ አለ
ለሁሉ ጤና ሰጭ
መስቀልህ መስቀልህ
ይሁንልኝ ክብሬ
ነፍሴ እስክታርፍ ድረስ
ወንዙን ተሻግሬ
2.
በመስቀልህ አገኘሁ
ፍቅርህን ምህረትን
ብሩህ የአጥቢያ ኮከብ
ሲያሣየኝ ብርሃንን
3.
መስቀልህ የአምላክ በግ
ይታያል በፊቴ
ከቀን ወደ ቀን እርዳኝ
አታርቀው ከኔ
4.
በመስቀልህ አጠገብ
ልጠብቅ ተስፋህን
ከሚያምረው ቦታ እስክደርስ
ተሻግሬ ወንዙን