1.
መልካም የደስታ አገር
ቅዱሳን ያሉበት
ቀኑ ጨለማን ያርቃል
ደስታም መከራን
የዘላለም ምንጭ ይፈልቃል
አበቦችም አይደርቁም
ይህ መልካም አገር ቅርብ ነው
የሰማይ ቤታችን
2.
ንጹህ የቅዱሳን አገር
ሰላም የሞላበት
ኃጢዓተኞች ተንኮለኞች
አይችሉም ሊወርሷት
በሮቹ ኃጢዓት ተንኮልን
ፈጽሞ አያስገቡም
የአምላክ በግ ተከታዮች
ይገባሉ ሁሉም
3.
ጥርጥራችን እናርቅ
የጨለማን ኃሣብ
ከንዓንን እንመልከት
በብርሃን አይናችን
ሙሴ ከቆመበት ሆነን
አገሩንም እንይ
የዚህ ዓለም ደስታ
ሁሉ አያታልለንም