1.
ፊት ለ ፊት ከክርስቶስ ጋር
ፊት ለፊት እንዴት ይሆን
በደስታ ባየሁት ጊዜ
የሱስ የሞተልኝን
ፊት ለፊትም አየዋለሁ
በሰማዩ ሰማያት
ክብርን ለብሶ አየዋለሁ
ፊት ለፊት አየዋለሁ
2.
አሁን በድካም አያለሁ
ጨለማ ስላገደኝ
ግን ክብሩ የሚታይበት
የተስፋው ቀን ይመጣል
3.
እንዴት ደስ ይለኝ ፊቱን ሳይ
ኃዘን ሕመም አልፎ ሳይ
ጠማማው መንገድ ሲቃና
ጨለማውም ሲጠፋ
4.
ፊት ለፊት ወይ መታደሌ
ፊት ለፊት ሳውቅና ሳይ
ፊት ለፊት ከመድኃኒቴ
ካፈቀረኝ የሱስ ጋር