1.
ጊዜያቱም ይሄዳል
ወራቱም ይመጣል
ወዳጆቻችንን ልናይ
በቀብር ያሉትን
ኦ ጌታ ሆይ ነፍሴን
አዘጋጅ ለዚያ ቀን
ኦ ጌታ በደምህ አንጻኝ
ኃጢዓቴንም አርቅ
2.
2. ወጀብም ይነሣል
ጥቂት ያንገላታል
በኋላ ዕረፍት ይገኛል
ለዚያ ጸጥ ያለ ቀን
አዘጋጀኝ ጌታ
ለዚያ ለታላቅ ቀን
በከበረው ደምህ አንጻኝ
ኃጢዓቴንም አርቅ
3.
3. በዚህ ዓለም ስንኖር እንቸገራለን
በዚህ ዓለም እናዝናለን
ከላይ ኃዘን የለም
አዘጋጀኝ ጌታ
ለዚያ ለታላቅ ቀን
በከበረው ደምህ አንጻኝ
ኃጢዓቴንም አርቅ
4.
4. ጥቂት ጊዜ ቀርቷል
ጌታችን ሊመጣ
ለኛ ሲል የሞተልንን
ከርሱ ጋር ሊያነግሠን
አዘጋጀኝ ጌታ
ለዚያ ለታላቅ ቀን
በከበረው ደምህ አንጻኝ
ኃጢዓቴንም አርቅ