ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #233h / Song #233h

የየሱስ ግሩም ፀጋ

Wonderful Grace of Jesus

ምድብ / Category: ወጣቶች / Young People
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የየሱስ ግሩም ጸጋ
ኃጢአቴን ሸፈነው
ምላሴስ እንዴት ትድፈር
ክብሩን ለመናገር
ሸክሜን ከላዬ አነሣ
እኔም ነጻ ወጣሁ
ባስገራሚው በየሱስ ጸጋ ድኛለሁ
ታላቁ የየሱስ ግሩም ጸጋ ከጥልቁ ባሕር የላቀ ነው ግሩም ጸጋው ይበቃኛል
ለኔ ይበቃኛል
ኃጢአቴን ሁሉ ያጠፋልኛል ኃፍረቴንም ይሰውረዋል
ለየሱስ ስም ክብር ይሁን
አሜን ለዘላለም
2.
የየሱስ ግሩም ጸጋ
ፈልጐ ያገኘኝ
በርሱ ይቅር ተብዬ
ለዘላለም ዳንሁኝ
ከግር ብረት ተፈታሁ
ነጻነት አገኘሁ
ባስገራሚው በየሱስ ጸጋ
ድኛለሁ
3.
የየሱስ ግሩም ጸጋ
እርኩሱን ያነጻል
ጸንቶ በቆመው ኃይሉ
ልጁ ያደርገዋል
ሰላም ለልቡ ሰጥቶ
ያወርሰዋል ክብሩን
አስደናቂው የየሱስ ጸጋ ይመስገን
100%
100%