1.
አንድን ታላቅ ሥራ በመፈለግ አትታክት
በሩቅ አገር መልካም ልትሠራ ባጠገብህ ባለው ሥራ
ታማኝ ሁንና
ባለህበት ማዕዘን አብራ
ባለህበት ማዕዘን አብራ
ባለህበት ማዕዘን አብራ
ከወደብ የራቀውን
ሰው እንድትመልሰው
ባለህበት ማዕዘን አብራ
2.
መከራ ተደቅኗል
ልታጠፋው ያሻል
በሩ እንዳይዘጋ ቸል ስትል እርዳታህን የሚሻ
አንድ ሰው ብቻ ቢሆን
አብራ ባለህበት ማዕዘን
3.
ለመክሊትህ ሁሉ ቦታ
አለው ጌታችን
ለንጋት ኮከብ ሥራ በእምነት ለችግረኛ ፍጥረቶች
ዘርጋ እጅህን
አብራ ባለህበት ማዕዘን
4.
ዕረፍት ለማግኘት
ከሰቀቀን ለማምለጥ
ወደ ቤታችን ስንገሠግሥ አይፈስም እንባ
በምታምረው ከተማ
ወደ ቤታችን እንገሥግሥ