ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #277h / Song #277h

ያምላካችን ታናሽ ጭፍራ

God's Children Have a Firm Foundation

ምድብ / Category: የልጆች / Children
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ያምላካችን ታናሽ ጭፍራ ጽኑ በሁሉ ሥፍራ በአምላክ ይታመናሉ
ሁሉን ከርሱ ያገኛሉ
2.
ልጆችም ባምላክ ተራራ ይኖራሉ ከርሱ ጋራ
እርሱም ልጆቹን ይጠራል ከነርሱ ጋራም ይኖራል
3.
ደስታ ቢሆን ወይም ጭንቀት
ልጁን ከርሱ እጅ አይነጥቅም ያ ወዳጅ በጹኑ እጁ
ጋሻ መክቷል ለልጁ
4.
የራሳችን ጠጉር ሁሉ በአምላክ ይቆጠራሉ
አምላክም ይመግበናል
በርሱ ፍቅር ደስ ይለናል
5.
ላንዳችን ቢሰጥ ቢነሣም አባትነቱን አይረሳም
ኃሳቡ ለጥቅማችን ነው
ለመላው ዘመናችን
6.
ደስ ይበልህ ታናሽ መንጋ አምላክህን አትዘንጋ
በርሱ ኃይል ጠላቶች ሁሉ ቢነሡብህ ይጠፋሉ
100%
100%