1.
ኦ የቤትልሄም ከተማ እንዴት ፀጥ ብለሻል
በጣም እንቅልፍ ተጭኖሽ ሳል ከዋክብት ያልፉሻል
ግን ጨለማው መንገድሽ ለዘላለም በራ
የዘመናት ተስፋ ምኞት ለዘላለም በራ
2.
ክርስቶስ ከማርያም ተወልዶ ሰበሰበ ሁሉን
መላእክት መዝሙር ዘመሩ ሲያንቀላፉ ሙታን
ያጥቢያ ከዋክብት ሁሉ ልደቱን ንገሩ
ምስጋና ይሁን ለእግዚአብሔር
ብላችሁ ዘምሩ
3.
እንዴት በፀጥታ መጣ
ግሩሙ ስጦታ
ለሰዎች ልጆች ተሰጠ የሰማዩ ጌታ
ኃጢዓት በሞላው ዓለም የሚሰማው የለም
ገሮቹ ግን ተቀበሉት
የሱስ ክርስቶስን
4.
ኦ የቤትልሄም ቅዱስ ልጅ
ና ና ወረድልን
ኃጢዓታችንን ፋቅልን
ስጠን መንፈስህን ሲያወሩልንም ሰማን መላእክት ልደቱን
ኦ ጌታችን አማኑኤል
ና ከኛ ጋራ ሁን