ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #114t / Song #114t

የልቤ አምላክ ሆይ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
እግዚአብሔርን ይሄ ነው ተስፋ ያደረኩት
ታማኝነቱን አይቼ እጄን ልቤን የሰጠሁት
ያለ አዋቂዎች ልቦና በሰዎች ተስፋ ያደርጋል
ግን እግዚአብሔር ብቻ ድህንነትን ያዘጋጃል
እጅግ ተቸግሬ ስማፀን አይተኸኝ
እኔ ከአንተ ጋር ነኝ አትፍራ እያልከኝ
በመጽናናት ሞልተህ ደስታን ታስታጥቀኛለህ
የልቤ አምላክ ሆይ የዘለዓለም ዕድል ፈንታዬ ነህ
2.
የተማሰው ጉድጓድ አፉን በእኔ ላይ አልዘጋም
ጉልበቴ ባለቀ ጊዜ ለብቻዬ አልተውከኝም
ስለ ትንሿ እምነቴ ከባለጋራ ተሟግተህ
የድል አምባ አስረገጥከኝ ውጊያውን ሁሉ ፈጽመህ
3.
ምሥጋናዬን እያዜምኩኝ በአንተ ደስ ይለኛል
በከንቱ በሚጠሉኝ ፊት ሞገስ አጐናጽፈኸኛል
ዓለም ብትሰርዘኝም የሕይወት መዝገብ አውቆኛል
እስከ መጨረሻው ድረስ ሕይወቴ በአንተ ይጸናል
100%
100%