አምላኬ (2x) ወደ አንተ እገሰግሳለሁ
ኃይልህን ክብርህን እንዳይ እሮጣለሁ
ፊትህን አሳየኝ ደስታን እጠግባለሁ
ምህረትህ ይብዛልኝ በሕይወት እኖራለሁ
1.
ገና ሌሊት ሳለ ከእንቅልፌ እነሳለሁ
የፊትህን ብርሃን ላይ እፈልጋለሁ
ነፍሴ እንደ ውኃ አንተን ትጠማለች
በቀንም በማታም ትናፍቅሃለች
2.
እጆቼን በሥምህ ወደ አንተ እያነሳሁ
በዘወትር ፀሎት ምሥጋና አቀርባለሁ
በሁለንተናዬም እገዛልሃለሁ
ምንጊዜም የአንተው ነኝ በቤትህ እኖራለሁ
3.
ሺህ ዓመት በሥጋ ከመኖር በከንቱ
እውነትህን አውቆ ይሻላል መሞቱ
መስቀልህን መያዝ መርጫለሁ እኔ
ይህ ነው ጌታዬ ሆይ የነፍሴ ውሳኔ