የሚቋቋምህ ማንም የለም
ፈቃድህ በእኛ ይሙላ ይፈፀም
ታላቅነትህም ይነገር
ጌታዬ ሆይ አንተ ብቻ ክበር (2x)
1.
ሕዝብህን ከምድር ዋጅተሃል
ታላቅ ሥራ ጀምረሃል
ሀሳብህ አይከለከልም
ፅድቅህ እውነትህ ይለምልም
2.
በየደረስንበት ስፍራ
ስራችንን አንተ ሥራ
እጃችን ሳይዝል ስይደክም
ዛሬም እንደ ወትሮ ቅደም
3.
ስለተነቀፈው ሥምህ
በምርኮ ስላለው ሕዝብህ
ይዘርጋ ያ ፅኑ ክንድህ
ዛሬም ይንሰራፋ ክብርህ
4.
ወድቀን በፊትህ ስንጮህ
ክንድህ ከፍ ይበል ጌታ ሆይ
ሰማይ ምድሩ ያከብርሃል
ሁሉም በፊትህ ይሰግዳል