ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #189t / Song #189t

ልጅነቴ አላለቀም

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ልጅነቴ ያላለቀ ነኝና ብላቴና
ሙሉ ሰው አድርገኝ ጌታ ቃልህን አብላኝና (2x)
1.
በግብዝነት ተሯሩጬም ከእውነትህም ተሳሰቼ
በስሜት ተገፋፍቼ የቃልህን ሙላት አጥቼ
እንዳልጠፋ በጠላት ተጠቅቼ
2.
ለጋነቴ እኔን አጋልጦኝ መከራውም አጠውልጐኝ
አውሎ ነፋስ አፍገምግሞኝ የአሸዋው መሠረት አዝሞኝ
ክፉኛ ገፍትሮ እንዳይጥለኝ
3.
ወተት ብቻ መጋቱን ትቼ አጥንቱንም ደግሞ በልቼ
እንደ ህጻን ማሰቤ ቀርቶ በጐልማሳነት ተተክቶ
ላይ እሻለሁ ሕይወቴ ተገንብቶ
100%
100%